20 የአፍሪካ ሃገራት በቀጣዩ ሳምንት የኮሮና ክትባቶችን እንደሚያገኙ የአፍሪካ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር አስታውቋል።
ይሁንና ኢትዮጵያ ከ20ዎቹ ሃገራት መካከል ስለመሆኗ ማዕከሉ ያሳወቀው ነገር የለም ተብሏል።
አፍሪካ ሲዲሲ 1 ሚሊዬን ክትባት በመጪው ሳምንት ወደ አህጉሪቱ እንደሚገባ አስታውቋል።
የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በቀጣዩ ሳምንት ለ20 የአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን እንደሚከፋፍል አስታውቋል፡፡
ክትባቶቹ በህንድ የተመረቱ የአስትራዜናካ ክትባቶች ናቸው ያሉት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ የመጀመሪያዎቹ ሚሊዬን ክትባቶች ከሳምንት አርብ ወዲህ ለሃገራቱ ይደርሳሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ክትባቶቹ ኤምቲኤን በተባለው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ድጋፍ የተገዙ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኤምቲኤን 7 ሚሊዬን ገደማ ክትባቶችን ለመግዛት የሚያስችል የ25 ሚሊዬን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ የተሻገረ ሲሆን ከ100 ሺህ በላይ አፍሪካዊያን ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።
ደቡብ አፍሪካ፤ግብጽ፤ሞሮኮ እና አልጀሪያ በአንጻራዊነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዜጎቻቸው በኮሮና ቫይረስ የተጠቁባቸው አገራት ሲሆኑ ኢትዮጵይ ከዚህ ረገድ 5ኛዋ አገር እንደሆነች የጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ መረጃ ይጠቁማል።
አዲስ አበባ
የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም