የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ህይወታቸው ያለፈው በኮሮና ቫይረስ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስቴር በተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን በህክምና ሞያና ሌሎች ዘርፎች በትጋት ሀገራቸውን አገልግለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በታላቁ ሰው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
በዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈተ-ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን በውጭ ግንኙነት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባል በመሆን እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ከድሆች ጓዳ የዘለቀ የሕክምና ድጋፍ በመስጠት ሀገራቸውን በፅናት ያገለገሉት ታላቁ ምሁር ናቸው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡
በሐረር ተወልደው በአዲስ አበባ እንደተማሩ እና እንዳደጉ የሚነገርላቸው የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ከአገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ከተለያዩ ተቋማት እና አገራት መሪዎች ተቀብለዋል።
የባህር ዳር ዩንቨርሲቱ የክብር ዶክትሬት፤የሩሲያ ታላቁ የአገሪቱን ሽልማት ከፕሬዘዳንት ቭላድ ሚር ፑቲን፤ከአሜሪካ ባዮግራፊካል ኢንስቲትዩት የሎሬትነት ማዕረግ እና ሌሎች የአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተቀብለዋል።
ኢትዮጵያ ቱዳይ በእኝህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አገር ወዳድ ሐኪም እና ዲፕሎማት ህይወት ማለፍ ማዘኑን እየገለጸ ለቤተሰቦች እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን መጽናናትን ይመኛል።
አዲስ አበባ
የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም