አዲስ አበባ ( ኢትዮጵያ ቱደይ) መጋቢት 30 ቀን 2016ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙትን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የኤግዚቢሽን ማእከል እና ገበያ ልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ አድርገው ሰየሙ
በከንቲባዋ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ ሌሎች ሶስት የቢሮ ሃላፊዎችን በቦርድ አባልነት መሰየማቸውን የሚገልጽ ሲሆን፡፡ የቀድሞው የቦድርድ ሰብሳቢ እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም ምከሩ በወ/ሮ ሊዲያ መተካታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ሶስት የቦርድ አባላት ተተክተዋል፡፡
መጋቢት 10 ቀን በከተማው አስተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ የኤግዚቢሽን ማእከል እና ገበያ ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ጥላሁን ታደሰ ከሃላፊነታቸው መታገዳቸው ይታወሳል፡፡