አዲስ አበባ ( ኢትዮጵያ ቱደይ) መጋቢት 19 ቀን 2016ዓ.ም
M-PESA ሳፋሪኮም ለባለፉት ሦስት ወራት ሲያካሒድ የቆየው ‘ተረክ በ M-PESA’ የሽልማት መርኃ ግብር መጨረሻ የሆነው የስድስተኛው ዙር ሽልማት አሰጣጥ እና የመርኃ ግብሩ መዝጊያ ስነ ስርዓት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ጊዮን ሆቴል መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናውኗል።
የመርኃ ግብሩ መጨረሻ በሆነው ስድስተኛ ዙር እድለኞች ከሁለት መኪኖች በተጨማሪ ሦስት ባጃጆች፣ 360 ስልኮች እና በሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ሰዓት እጣዎችን ተሸልመዋል።
በዚሁ የሽልማት መርኃ ግብር ላይ አንደኛውን እጣ ሚትሱቢሺ አትሬጅ መኪና የተረከቡት ደንበኛየአሳሳ ከተማነዋሪው ደስታ አማን ሙዲ ሲሆኑ፣ የወኪሎች እና የነጋዴዎች አሸናፊ የጅግጅጋው ይድረሱ ታደለ ታኒ ሆነዋል።
በመርኃ ግብሩ አጠቃላይ ለእድለኞች የተሸለሙ መኪኖች ቁጥር 4 ሲሆን፣ 24 ባጃጆች፣ 2160 ስልኮች እና በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ ያላቸው የአየር ሰዓት ሽልማቶችም በስድስቱ ዙር ለባለእድለኞች ተሸልመዋል።
የM-PESA ሳፋሪኮም የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ስትራቴጂክ አጋርነት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ክፍሌኃ/እየሱስ በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር “
የM-PESA ሳፋሪኮም ተረክ የእድለኞችን ሕይወት ከመለወጡ በተጨማሪ የገንዘብ ክፍያን እና ዝውውርን ያቀለለ፣የM-PESA መተግበሪያን በኢትዮጵያ ዙሪያ ያስተዋወቀ እና የብራንዱን ታዋቂነት ከፍ ያደረገ መርኃ ግብር እንደነበረ የM-PESA ሳፋሪኮም የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ስትራቴጂክ አጋርነት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ክፍሌ ኃ/እየሱስ ገልፀዋል።
በመርሃ ግብ ሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ተሸልመዋል።