አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱ ደይ)ሚያዝያ 08 ቀን 2016
በምዕራብ ትግራይ በፀለምቲ አካባቢ እና በደቡብ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች በአማራ ታጣቂዎች የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ ታደሰ ወረደ ገለጹ።
“የመጀመሪያው እርምጃ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችን ማፍረስ እና የተቋቋሙትን ህገ-መንግስታዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ማፍረስ ነው” ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ፤ “የፍትህ ስርዓቱን ወደነበረበት መመለስ” በተከታይነት ይሰራል ብለዋል።

ጄኔራሉ የታጠቁ ሃይሎች ከፌዴራል ሃይሎች ጋር መጠነኛ ግጭት በመፍጠር ሂደቱን እያስተጓጎሉ መሆናቸውንም አብራርተው የፕሪቶሪያ ስምምነት ግጭት እንዳያገረሽ በሚከላከል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ እንደገለጹት የፕሪቶሪያ ስምምነት የግዛትን ጨምሮ ሁሉም አለመግባባቶች በህገ መንግስቱ መሰረት መፈታት እንዳለባቸው መደንገጉን አስታውሰዋል።
በራያ አላማጣ አካባቢ የህወሓት ታጣቂዎች ወረራ መፈጸማቸው መዘገቡን ተከትሎ ነው ይኽ መግለጫየተሰጠው።