ተቋሙ ከዓለም አቀፉ ቪዛ ኩባንያ ጋር ስትራቴጂካዊ ሲል የጠራዉ ስምምነት በሃገሪቱ የመጀመሪያውን ቨርችዋል ቪዛ ካርድ እንዲሁም ሀዋላን በእጅጉ የሚያዘምኑ የቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት አገልግሎቶች ለማቅረብ የሚያስችል እንደሆነም ገልጿል ።
በሃገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ደንበኞች የዋሌት ቨርቹዋል የቪዛ ካርድ እንዲኖራቸው የሚያስችል እንዲሁም ነባሩን የሃዋላ አገልግሎት በእጅጉ የሚያዘምኑ ቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት (VISA Direct and telebirr Remit services) የተሰኙ የተሰኙ የአለም አቀፍ ገንዘብ ማስተላለፊያ ሀዋላ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን አብራርቷል ።
የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የቴሌብር ቨርችዋል ካርድ ቁጥርን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ወደ ሀገርቤት ለማስተላለፍ የሚያስችላቸው ነዉ ብለዋል።
የቴሌብር ደንበኞቹን ቁጥር ብዛት 47.55 ሚሊዮን በላይ የሆነዉ ተቋሙ ዛሬ ያደረገው ስምምነት ደንበኞች የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር እንዲያገኙ እንዲሁም ከመደበኛው ሃዋላ የተሻለ አማራጮች በቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።