የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማህበራዊ ገጽ ተጠለፈ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ባሰራጨው መረጃ የፌስቡክ ገጼ ተጠልፏል ብሏል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ዛሬ ለሁሉሜ ሚዲይዎች ባሰራጨው መግለጫ እንደተመላከተው÷ የፌስቡክ ገጹ ከተቋሙ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡
በመሆኑም በኢንስቲትዩቱ የፌስቡክ ገጽ የሚወጡ መረጃዎች ከተቋሙ ዕውቅና ውጭ በመሆናቸው÷ ሕብረተሰቡ ከተሳሳቱ መረጃዎች እራሱን እንዲጠብቅም አሳስቧል፡፡
ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በየዕለቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የሚታወቀው ይህ ኢንስቲትዩት ከዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ ያልተገቡ ቪዲዮዎች በመሰራጨት ከላይ ናቸው።
ይሁንና የኢንስቲትዩቱ የፌስቡክ ገጽ በማን እንደተጠለፈ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።
የኢትዮጵያ በይነ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወይም ኢንሳ የመንግስት ተቋማት ማህበራዊ ድረገጾቻቸውን ከጠላፊዎች እንዲጠብቁ ማሳሰቡ ይታወሳል።
እንደዚህ ተቋም መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ ላይ የበይነ መረብ ጥቃቶች እየጨመረ የመጣ ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት ብቻ 3 ሺህ ገደማ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን ገልጿል።