አዲስ አበባ ( ኢትዮጵያ ቱዳይ ግንቦት 15፣ 2016 ዓ.ም
እ.ኤ.አ ከ 2008 ወዲህ ወይም ከ16 ዓመት በኃላ ነው ዋይት ሃውስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ መሪ በዚህ ደረጃ ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው።
አሜሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፍ ያለ አቀባበል እና ከፍተኛ የቀድሞና የአሁን ባለስልጣናት በተገኙበት ልዩ እራት ግብዣ እንደተደረገላቸው ታውቋል።
ከፕሬዜዳንት ጆ ባይደንና ከሌሎች ባለልሰጣናት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉም ሲሆን ሁነኛ ስምምነቶችም ከአሜሪካ መንግሥት ጋር መፈራረማቸው ተሰምቷል።
ሩቶ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ጋርም ተገናኝነትው መክረዋል።
በሌላ በኩል ፥ ኬንያ የሀገሪቱን የጸጥታ ስራዎች እና የሰላም ማስከበር ተልእኮዎቿን ለማሳደግ 16 በአሜሪካ የተሰሩ እጅግ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ልትቀበል እንደሆነ ” ሲትዝን ቲቪ ” ዘግቧል።
ይህ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዋሽንግተን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ለኬንያ ካበረከቱት መልካም ነገሮች አንዱ ነው ተብሏል።
ሂሊኮፕተሮቹ እ.ኤ.አ ከ2024 እስከ 2025 መጨረሻ ናይሮቢ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋይት ሀውስ አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኬንያ በመስከረም ወር 150 ” M1117 ” የታጠቁ እጅግ ዘመናዊ የደህንነት ተሽከርካሪዎችን ትቀበላለች።