አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱደይ) ግንቦት 22፣ 2016 ዓ.ም ፦ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን በጠቅላላ ከዋለው ገንዘብ አኳያ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ያበረከተው አስተዋፅዖ ከ1 በመቶ በታች መሆኑ ተሰምቷል።
ግዙፉ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክተው ገለፃ ያደረጉት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 96 በመቶ መድረሱንና በመጪው እስከ ጥር ወር 2017 ዓ.ም. ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

ኢንጅነር ክፍሌ አያይዘውም እንደተናገሩት ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ከዲያስፖራው የተደረገዉ ከ 1 በመቶ በታች መሆኑና ይህም ከተጠበቀው አንፃር አነስተኛ ነዉ ብለዋል።
እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዋለው 192 ቢሊዮን ብር ውስጥ የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ያበረከተው 1 ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑ ነዉ የተገለፀው ።
ይህ የተነገረዉ ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ከሁለት ዓመት በፊት ያበለጸገውን መተግበሪያ በአዲስ መልክ አሻሽሎ ማቅረቡን በትላንትናው ዕለት ባሳወቀበት መድረክ ነው።