አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱደይ) መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል እና መቆጣጠር ላስመዘገበችዉ ዉጤት እዉቅና መስጠቱ ተገለጸ።
እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ መሆኑ ተጠቁሟል።
በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ያስመዘገበችው ውጤት እውቅናውን እንድታገኝ እንዳስቻለት ተገልጿል።
በአሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማቱን አበርክቷል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA77) ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን መቀበላቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።