አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱደይ) መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም
የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣዉ አዲሱ መመሪያ “ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎችን ለመወሰን” የሚል ሲሆን ይህም የትምህርት፣ የጤና እና የአደጋ መከላከል ስራዎችን ለመደገፍ ዓላማ ያለዉ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህ መመሪያ ዉስጥ ከውጪ የሚገቡ ቁልፍ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት ዕቃዎች፣ ለምሳሌ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፖሊስ ሃይሎች እና የብሄራዊ መረጃ አገልግሎቶች መሳሪያዎች፣ ከቀረጥ ነጻ የሆኑ እቃዎች ዝርዝር መካከል ይገኝበታል ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ለማድረግ ዓላማ ባደረገዉ መመሪያ ቁጥር 1023/2024 መሰረት ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አዛውንቶችን እና አካል ጉዳተኞችን የሚረዱ ድርጅቶችን ጨምሮ ለመንግስት ተቋማት የተበረከቱ እቃዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ ተብሏል።
የጉምሩክ ኮሚሽኑ ከቀረጥ ነፃ የወጡ ዕቃዎችን አጠቃቀም በቅርበት ተከታትሎ የሩብ ዓመቱን ሪፖርት ለገንዘብ ሚኒስቴር እንደሚያቀርብ ተገልጿል።