አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱደይ) ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓም
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በግጭት እና በተለያየ የተፈጥሮ ችግሮች የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸውን ባወጣው ሪፖርት ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግጭት በተፍጥሮ እና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት 5,568 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል ብሏል፡፡
በአማራ ክልል 4178፣ በትግራይ ክልል 648፣ በኦሮሚያ ክልል 402፣ በሶማሌ ክልል 195፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 50፣ በጋምቤላ ከልል 40፣ በአፋር ክልል 26፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትጵያ ክልል 8 በአጠቃላይ 5,568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስረድቷል፡፡
በዚህም የዜጎች ትምህርት የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና የህጻናት የአካል ጉዳተኛ እና የአረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሃዋሪያ ተናግረው ይህን መብት መንግስት እንዲያስከብር ጠይቀዋል፡፡
ኮሚሽነር ርግበ የትምህርት መብት በእጅጉን እየተጣሰ ነው ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል ፡፡
የትምህርት መብት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን ከግጭት አወድ በወጡ ማለትም በትግራይ በአፋር እና በከፊል በቤኒሻንጉል ጉሙዝም እየተጣሰ ነው ሲል ኢሰመኮ አስረድቷል፡፡