አራት ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ተደራርበው ጅቡቲ መግባታቸው ታውቋል።
አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱደይ) ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
ሁሉም ተሽከርካሪዎች በአስቸኳይ ወደ ማዳበሪያ ማጓጓዝ እንዲገቡ ታዘዘ
ከትላንት እሁድ ሰኔ 23 ጀምሮ የትኛውም ከጅቡቲ የሚነሳ የጭነት መኪና ከማዳበሪያ ውጭ መጫን እንደማይች መንግስት ለትራንስፖርት ማህበራት እና የግል አንቀሳቃሾች አስታውቋል።
ማዳበሪያ የማጓጓዝ ዘመቻ መታወጁን የገለፁት ምንጮች። በቀጣዩ 15 ቀን ተሽከርካሪዎች በሙሉ ማዳበሪያ ወደ መሃል አገር ያጓጉዙ መባሉን ጠቅሰዋል።
ትእዛዙ የመጣው በተመሳሳይ ቀን ማለትም ትላንት ሰኔ 23 ቀን እንደሆነ የታወቀ ሲሆን።
ሌላ ጭነት የያዙ ተሽከርካሪዎች ጭነቱን በማውረድ ማዳበሪያ እንዲያጓጉዙ መታዘዙ ታውቋል።
ከማዳበሪያ ውጭ ይዘው ወደ አገር ለመግባት የሚሞክሩ ተሽከርካሪዎች ካሉ ጉምሩክ እንደማያስተናግዳቸው ይወቁት መባሉን ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል።
ካፒታል ባገኘችው መረጃ ባለፈው ሳምንት በCIF ግዥ የተፈፀመበት ማዳበሪያ የያዙ 4 መርከቦች ተደራርበው ጅቡቲ ገብተዋል።
ይህም የጭነት ማጓጓዝ ሂደቱ ላይ ጫና የሚፈጥር ነው የሚሉት ምንጮች ባለፉት ጥቂት አመታት የመርከቦች አገባብ የተናበበ መሆኑ በርከቦች ቆይታ እና ጭነት ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ሂደት ከፍተኛ መሻሻል ታይቶበት ነበር።
Dawit, [Jul 1, 2024 at 8:01:42 PM]:
Seeds for the Future 2024 Welcomes Ten Ethiopian Students to Morocco
…