አዲስ አበባ ( ኢትዮጵያ ቱደይ) መጋቢት 16፤2016 ዓ.ም.)
ካፒታል በተመለከተዉ እና ለኩባያዉ ሰራተኞች ከዋና ስራ አስፈፃሚው ዴቭ ካልሁን በተላከዉ ደብዳቤ ላይ የአላስካ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 1282 አደጋ ለቦይንግ “ወሳኝ ለውጥ የተደረገበት ወቅት” እንደነበር እና ድርጅቱ የበለጠ የደህንነት እና የጥራት ማረጋገጫዎችን ለመስራት በሚፈልግበት በዚህ አመት ኩባንያውን እንደሚለቅ” ተናግሯል።
የቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቭ ካልሁን የኩባንያዉን የወደፊት እጣ ፈንታ በሚመለከት ለሰራተኞች በላከላቸዉ በዚህ ደብዳቤ ከዳይሬክተሮች ቦርድ ጋር ለተወሰነ ጊዜ በመወያየት በቦይንግ ውስጥ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽግግር ለማድረግ ትክክለኛውን ጊዜ እያሰብኩ ነበር ያሉ ሲሆን በዚህም በድርጅቱ በዋና ስራ አስፈፃሚነት የቆይታ ጊዜ የመጨረሻ አመት እንዲሆን መወሰኑን እና ይህን ውሳኔውን ለቦርዱ ማሳወቁን ተመልክተናል ።
በደብዳቤዉ “በዚህ አመት መጨረሻ ከዋና ስራ አስፈፃሚነት ለመልቀቅ ያደረኩት ውሳኔ ቦርዱ የተዘጋጀለት እና በአመራር እና በአስተዳደር ደረጃ በርካታ ለውጦችን የሚያስገኝ ነው” ማለቱን ካፒታል ተመልክቷል።
ከጃንዋሪ 2020 ጀምሮ የቦይንግ ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት የ66 ዓመቱ እና አሜሪካዊ ባለሀብት ዴቭ ካልሁን
ቀደም ሲል የቦይንግ ሊቀመንበር ሆኖ ማገልገሉን መረጃዎች ያመልክታሉ ።