አዲስ አበባ ( ኢትዮጵያ ቱደይ ) የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ በትላንትናው ዕለት መቋረጡ ይታወቃል ።
ዉሉ ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ተቋርጧል ያለዉ ፐርፐዝ ብላክ ዉላችን በዉልና ማስረጃ መፅደቅ ሲገባዉ በቢጂአይ በኩል ይህ ሳይሆን ቀርቷል ሲል ከሷል ።
ለሂደቱ መቋረጥ በምክንያትነት የተነሣው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ
የቢጂአይን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭን አስመልክቶ በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ኩባንያው አስታውቆ ነበር።
ፐርፐዝ ብላክ ለህንፃዉ ቅድመ ክፍያ 1 ቢሊዮን 150 ሚሊዮን ክፍያ መፈፀሙን አስታዉቋል።
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነትና አላሳየም ቢልም ፐርፐዝ ብላክ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ቢጂአይን ተጠያቂ በማድረግ በሁለተኛ ዙር ለክፍያ የተዘጋጀውን 2 ቢሊዮን 500 ሺህ ብር በመፈፀም ዉሉን በድጋሚ መዋዋል ፍላጎት አለኝ ብሏል።
ማንም ከመሬት ተነስቶ የሚያፈርሰዉ ተራ ዉል አይደለም ያለዉ የፐርፐዝ ብላክ ዋና ቦርድ ሰብሳቢ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለቢጂአይ በወሎና ማስረጃ ለመፈራረም ጥያቄ ቢቀርብም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርቷል። ነገር ግን በድጋሚ ዉሉን የማይፈረሙ ከሆነ ይህ ጉዳዩ ወደ ፍርድቤት ያመራል ሲሉ ተደምጠዋል።