6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ #Ethiopiaelection
6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከማንኛውም የደህንነት ስጋት ነጻ መሆኑን መንግስት አስታወቀ።
ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ እና ስጋት በሚል በአዲስ አበባ መክሯል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብሳቢነት የተካሄደው ይህ ስብሰባ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ምርጫ ከማንኛውም የደህንነት ስጋት ምን ያህል ነጻ ነው በሚለው ሀሳብ ላይ ተወያይቷል።
ውይይቱ በማዕከላዊ ዕዝ የሁኔታ ክትትል ክፍል ውስጥ ይፋ የተደረገው የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት አገልግሎት የምርጫ ደህንነት መድረክ በምርጫ ደህንነት ዘርፍ የተከናወነውን ዝግጁነትን አጉልቶ ያሳያል።
በተጨማሪም ውይይቱ የደህንነቱ ዝግጁነት በሁሉም የሀገሪቱ ማእዘናት ላይ አካላዊ ኃይል ማሰማራትን እንዲሁም የሳይበር ደህንነት ማሻሻያዎችን የተመለከቱ ስጋቶችን ማክሸፍን አጠቃሏል።
በመላው የፌዴራል እና የክልል ማዘዣ ጣቢያዎች ባሉ የመረጃ መጋራት መሳሪያዎች፣ የሳተላይት ቁጥጥር ስርዓቶች እና የድሮን ቴክኖሎጂ ለዚሁ ዝግጅት መሰማራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ገልጿል።
6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከ670 በላይ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ውጪ በቀሪዎቹ የአገሪቱ ቦታዎች ለ509 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ47 በላይ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ።
ብልጽግና ፓርቲ፤የኢትይጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፤እናት እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲዎች በምርጫው በአንጻራዊነት የተሻለ ፉክክር ያደረጉ ፓርቲዎች ናቸው።
በነገው ዕለትም በአዲስ አበባ፤አማራ ክልል ፤ድሬዳዋ እና ደቡብ ክልል ምርጫው የተሻለ ፉክክር የሚደረግባቸው አካባቢዎች ናቸው።
ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ