
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአምስት ታላላቅ ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳውን ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ።
ፓርቲው በነገው ዕለት የምርጫ ቅስቀሳ አካሂድባቸዋለሁ ያላቸው ከተሞችም አዲስ አበባ ፣ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች ናቸው።
ፓርቲው በነዚህ አምስት ከተማች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ ለአትዮጵያ ቱዴይ አስታውቋል።
ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በደብዳቤ ማሳወቁንም ገልጿል።
የዘንድሮው አገር አቀፍ ምርጫ ከግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
አዲስ አበባ
የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም