ከሙሼ ሰሙ
አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ተደይ) መስከረም 19 ቀን 2017 ዓ.ም
በብቸኝነት ያለ ተወዳዳሪ አገልግሎት ሰጭ ስለሆኑ ብቻ በቂ፣ አሳማኝ ምክንያት ሳይኖር እጅግ ለዛገ፣ ለተንቀርፈፈና ለሙስና ተጋላጭ ለሆነ አገልግሎት ከ150% እስከ 700 % ጭማሪ ማድረግ ሕዝብን ከማስመረር ውጭ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም። የዚህ ዓይነቱ መብትና ስልጣን ከምን አመክንዮ ሊመነጭ እንደሚችልም ለመረዳት አዳጋች ነው።
የመንጃ ፈቃድ እድሳት፣ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ)፣ መንጃ ፈቃድ ለጠፋበት (የጠፋበት እንጂ ሌባ ለሰረቀው ተመኑ አልተገለጸም)ና ለቦሎ ወዘተ የሚሰጠው አገልግሎት ካርድ፣ ወረቀትና ተለጣፊ አትሞ ከመስጠት ውጭ የቴክኒክ፣ የብቃት ወይም የእውቀትና የክህሎት አገልግሎት የለውም። የጭማሪው መንስኤም አልተገለጸም። አዲሱ የኢኮኖሚ ፓሊሲ ያሰሸከተለው የእቃ ዋጋ መናር፣ የደሞዝ ጭማሪውን በራስ ገቢ መሸፈን ወይስ ሌላ ?
የወረቀቱም ሆነ የካርዱ ወይም የተለጣፊው ጥሬ እቃ ለማስመጣትም ሆነ ከገበያ ለመግዛት ዋጋው ከ10 ብር አይበልጥም። ኮምፒዩተር ከፍቶ ስም አጣርቶና ነባሩ መንጃ ፈቃድ ሕጋዊ መሆኑን አረጋግጦ ካርድ አትሞ ለመስጠት (ተጓዳኝ ወጭ ጨምሮ) 100 ብር ለማያወጣ አገልግሎት 900% ትርፍ መጠየቅ ምንም ዓይነት አመክንየ ሊቀርብበት አይችልም። ከስልጣን (Authority) በስተቀር ግለሰብ ሱቅ ከፍቶ ሊሰራው የሚችለው የተለየ እውቀትና ብቃት የማይጠይቅ ስራ ነው።
የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል በተመጣጣኝ ዋጋ ለማገልገል የተቋቋሙ ናቸው። ከመርሆዎቻቸውም ውስጥ ተደራሽነት፣ ቀልጣፋ፣ ለተመጣጣኝ አገልግሎት ተመጣጣኝ ዋጋ መጠየቅ ዋነኞቹ ናቸው ።
ከተሽከርካሪ ጋር የተያያዘ አገልግሎት ወረቀት፣ ካርድና ተለጣፊ ከማተምና የጽሕፈት አገልግሎት ከመስጠት ያለፈ ትርጉም ያለው ስራ አይጠይቅም። ልክ እንደ ሸቀጥ ነጋዴ በዘፈቀደና እጥረት ስለተፈጠረ ወይም ብቸኛ አገልግሎት ሰጭና አቅራቢ ስለሆነ የፈለጉትን ዋጋ መቆለል ምን ታመጣላችሁ መሆን አለበት። በቸኛ አረጋጋጭ መሆን ንጉስ መሆን ማለት አይደለም።
ተሽርካሪ ያለው ሁሉ አቅም አለው ማለት አይደለም። በዚህ ጣራ በነካ ኑሮ ዋጋ መቆለል የእለት ጉርሳቸው ከዚህ አገልግሎት ጋር የተያያዘ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች መርሳት ነው። እንደዚህ ዓይነት የዘፈቀደ የዋጋ ጭማሪ በነጋዴውም ሆነ በሹፌሩ ዘንድ ሊቀሰቅስና ሊያቀጣጥል የሚችለውን የዋጋ ጭማሪ ማጤን መልካም ነው። አንተ ዋጋ አትጨምር እኔ ግን እንደልቤ ዋጋ እጨምራለሁ ማለት ውጤቱ በገዛ ራስ እግር ላይ ጥይት የመተኮስ ያህል ነው።
ሰሞኑን እያወዛገበ ያለው የመንግስታዊ ተቋማት የአገልግሎት ተመን ጭማሪ ከመንስኤው ጀምሮ ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር የማይጣጣምና ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሚያስደነግጥ እየሆነ ነው