አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ ቱደይ) መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም
ቀድሞ የተዘጋጀ በቂ የኢንቨስትመንት መሬት አሰጣጥ ፣ ከመጠን ያለፉ የካሳ ጥያቄዎች አና የካሳ አሰጣጥ አስተዳደር ችግሮች ለባለሀብቶች የልማት መሬት አቅርቦት እንዳያገኙ ተግዳሮት መሆኑን በዘፉ ላይ የተደረገው የፓሊሲ ሰነድ አመላክቷል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የአዉሮፓ ቻምበር ለባለሀብቶች የመሬት ልማት አቅርቦት ላይ ያተኮረውን የፖሊሲ ሰነድ በዛሬው ዕለት ይፋ ማድረጉን አስታዉቋል ።
ሰነዱ በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት መሬት ከማግኘት ጋር በተያያዘ የግሉ ሴክተር ላይ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በመለየት የዉጪ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ መሳብ ዓላማ እንዳለው በወቅቱ ተገልፆዋል።

በኢትዮጵያ መንግስት ሊታሰብባቸዉ የሚገብ የዉሳኔ ሀሳቦች የቀረብበት ይህ ሰነድ ” ቀልጣፋ የመሬት አስተዳደርን ማስፈን ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ልማትን የሚያበረታታ ግልፅነትና ወጥነት ያለዉ ፖሊሲ መዘርጋት ቀዳሚዉ መሆኑን ተመልክቷል ።
“የመሬት ተደራሽነት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉጪ ላሉ ባለሀብቶች የመሬት አሰጣጥ ሂደትን ማመቻቸት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ሰነድ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች የልማት መሬት ከማግኘት ጋር ተያይዞ ስለሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች አስቀምጧል።